ጸናጽል ድምጹ
መልካም
የሆነ
የምስጋና
ዕቃ በመሆኑ
ከቀደሙት
ሌዋውያን
አሁን
እስካሉት
የሐዲስ
ኪዳኑቤተ
መቅደስ
መዘምራን
፣ከቀደመው
የሙሴ
ድንኳ
ዛሬ እስከደረስንበት
ቅድስተ
ቅዱሳን
ድረስ
በእግዚአብሔር
ፊት ይዘነው
የምንቆም
የምስጋና
ዕቃ ነው፡፡
ምስጋናችንም
ሆነ ዘፈናችን
ያለከበሮና
ጸናጽል
ምን ውበት
ሊኖረው
ብለን
እንጀምራለን?
አንጀምረውም፤
የሊቃውንቱ
መዳፍ
ያለ ጸናጽል
አይንቀሳቀስም፣ቅኔ
ማኅሌቱም
ያለ ከበሮ
አይደምቅም
፤ እንደ
ጾመ ኢየሱስ
ያለ ጨካኝ
ቀን ካልወረደበት
በስተቀር
ቅኔ ማኅሌት
ከነዚህ
ነገሮች
አይለይም፤
ይገርማል!
ዳሩ ግን አንድም
ቀን ቢሆን
በዚህ
ሁሉ የአገልግሎት
ዘመናቸው
ወደ ቤተ መቅደስ
ገብተው
ለስጋውና
ለደሙ
ክብር
በሚደረገው
አገልግሎት
ተሳትፈው
አይተናቸው
አናውቅም
ጥንትም
ሆነ ዛሬ ከውጭ
ብቻ ነው -አገልግሎታቸው፤
ቅዱስ
ጳውሎስ
የባዶኅይወት
ተምሳሌት
አድርጎ
ተጠቅሞበታል
‹‹የሰውን
ሁሉ ልሳን
ባውቅ
፣በመላዕክትም
ቋንቋ
ብናገር
ፍቅር
ግን ከሌለኝ
እንደሚጮኽ
ነሐስ
እንደሚንሿሿም
ጻናጽል
ነኝ››1ቆሮ 13÷1ይላል
ይህን
ስመለከት
ከልጅነቴ
ጀምሮ
በቤተ
መቅደሱ
ያደገች
ነፍሴን
አሰብኩና
እስራኤል
ሲማረኩ
‹‹ጽዮንን
ባሰብናት
ጊዜ አለቀስን››ብለው እንደተናገሩ እኔም ለተማረከችውና ባዶዋን ለቀረችው ጽዮን ሰውነቴ አለቀስኩላት ከኔ በቀር ጽዮን ሰውነቴ ባለተስፋ ምድር መሆኗን ማን ያውቅላታል? የተገባላትንስ ቃል ኪዳን ከኔበቀር ማን ያውቅላታል?
ስለዚህ ደጋግሜ በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ሆኘ ምርር ብየ አለቀስኩላት ደግሜ ደግሜም እንዲህ አልኳት እንደሚጮኽ ነሐስ፣ እንደ ሚንሿሿም ጸናጽል ነሽ አልኳት
እስኪ
አስቡት
!ያለኔ
ማኅሌቱ
አይጀመር፣ዝማሬው
አያምር
፣የሊቃውንቱ
ጉሮሮ
አይከፈት፣
ሽብሻቧቸው
አያምርበት
፣እጃቸው
ያለኔ
አይንቀሳቀስ፣ቅኔው
መወድሱ
ያለኔ
አይፈስ፣
ስብሐተ
ነግሑ
አይደረስ፣አርያሙ
አይዜም፣
ዋዜማው
አይቆም
እስኪ
ንገሩኝ
ምኑ ነው ያለኔ
እሚያምረው፤
በየትኛው
አገልግሎት
ነው እኔ እማልገባው፤
የትኛውስ
ሊቅ ነው ያለኔ
በእግዚአብሔር
ምስጋና
ላይ የተገኘው
፤ ጥንትም
ሆነ ዛሬ እኔ ለዚች
ቤተ መቅደስ
አገልግሎት
አስፈልጋለሁ
፡፡