1ኛ ነቢያትና ሐዋርያትን
ነቢያትና ሐዋርያት በዘመን፣
በግብር፣ በክብር የማይገናኙ አባቶቻችን ናቸው፤ ነቢያት የምንላቸው ከአዳም እስከ ዮሐንስ መጥምቅ ያሉትን ሲሆን ሐዋርያት የምንላቸው
ደግሞ ከክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያን የምሥራቹን እንዲነግሩ የተላኩ አባቶቻችንን ነው፡፡ በእርግጥ ሐዋርያ የሆነ
ነቢይ አናገኝም እንጅ ነቢይ የሆነ ሐዋርያ ማግኘት ይቻላል፤ ለነቢያት የተሰጠው መንፈሰ ረድኤት ሲሆን ለሐዋርያት የተሰጠውን መንፈሰ
ልደት ማግኘት ለነቢያት አልተቻላቸውም ሐዋርያት ግን በመንፈሰ ረድኤት ላይ መንፈሰ ልደትን ጨምረው መያዝ ሰለተሰጣቸው ሁሉንም አንድ
አድርገው ይዘዋል፤ የመጠን ልዩነት ይኖረው ይሆናል እንጅ ሐብተ ትንቢት ያልተሰጠው ሐዋርያ የለም፤ ለዚህም ነው ሐዋርያው ስለዚህ
ዘመን ሲናገር‹‹በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጠን›› ዮሐ1÷18 ሲል አጉልቶ የተናገረው፡፡
በዚህ ምድር ላይ የእግዚአብሔርን
መንግሥት በመፈለግ እንደ ነቢያት ብዙ ድካም የደከመ ሊኖር አይችልም፤ ለዚህ ነው ሊቃውንቱ ነቢያትን በክረምት ገበሬ ሐዋርያትን
በበጋ ገበሬ የሚመስሏቸው፤ የክረምት ገበሬ ላዩ ውሃ ታቹ ውሃ ሆኖበት በጭቃ ወጥቶ በጭቃ ይመለሳል ሲገባም ሚስቱ ጎመን ጠምቃ ታቆየዋለች
ያን በልቶ ደስ ሳይለው ይተኛል፤ ነቢያትም ዓለምን በጣዖት አምላኪ ነገሥታት በነቢያተ ሐሰት ስብከት ሲንገላቱ ይኖራሉ ሲሞቱም ሲኦል
እንጅ ገነት መግባት አይችሉም፤ የበጋ ገበሬ ግን በደረቅ ወጥቶ፣ እሸት በልቶ፣ ተደስቶ ይመለሳል እቤቱ ሲገባም እንጀራው በሌማት፣ጠላው
በማቶት ሲቀርብለት ደስ ብሎት ይመገባል ሐዋርያትም ልጅነት አግኝተው ለማስተማር ተልከዋል፣ በሄዱበት ተዓምራት እንዲያደርጉ፣ልጅነትን
እንዲሰጡ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል ሌሊት ሞታቸው ሲደርስም መንግሥተ ሰማያት ተከፍቶ ይቆያቸዋል፤
ቅዱስ ያሬድም
ስለነቢያትና ሐዋርያት ሲናገር ‹‹ኖትያት ነቢያት ራግናት ሐዋርያት›› በማለት ነቢያትን በዋናተኛ ሐዋርያትን በጀልባ ቀዛፊዎች መስሎ ይናገራል፤ ከዋናተኞች ይልቅ ቀዛፊዎች ድካም የለባቸውም፤ ዋናተኞች ውሃው አጥልቋቸው፣ መተንፈስ ተስኗቸው አንዳንዶቹ ዳር ይደርሳሉ አንዳንዶቹም በድካም በውሃው ውስጥ ጠልቀው ይቀራሉ፤ ቀዛፊዎች ይሄ ሁሉ የለባቸውም ምናልባት ስጋታቸው ማዕበል ሞገድ ነው እንጅ ሌላ ስጋት አይኖርባቸውም፤ ጀልባዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ለነቢያት በተስፋ እንጅ በአካል ያልተጨበጠች ጀልባ ናት፤ ሐዋርያት ተሳፈሩባት ባሕር የሚመስለውን ዓለም ተሻገሩባት፤ የነቢያት ድካም ጀልባዋ ካለችበት ለመድረስ ነበር ሳይደርሱ ሞት ቀደማቸው፤

ነቢያት የደከሙትን ድካም ባይጠቀሙበትም ለልጆቻቸው ጥቅምን አስገኝቶላቸዋል፤ ሐዋርያት የገቡት በነቢያት ድካም ነውና፤
አንዳንድ ጊዜ አንዱ የዘራውን ሌላው ያጭደዋል ነቢያትም የዘሩትን የትንቢት ዘር ሐዋርያት አጭደውታል፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ወንጌል
የነቢያት ዘር ናት ዳሩ ግን ዘሩት እንጅ አፍርቶ ፍሬ እስኪያፈራ መቆየት ባለመቻላቸው ፍሬውን የበሉት ደቀ መዛሙርቱ ናቸው፡፡