>

Monday, 22 June 2015

የሠሩኝ እጆች

                      
ያለንባት ምድር ትናንትና ሌሎች ሰዎች ነበሩባት፤ አንዳንዶቹ ሠርተዋት አንዳንዶቹ ደግሞ አፍርሰዋት ሂደዋል፡፡ እጣ ፋንታዋ ይህ ነውና ያበቀለችውን አብልታ፣ ያፈለቀችውን አጠጥታ፣ ከሆዷ የወጣውን አልብሳ ያሳደገቻቸው ሁሉ ጥቂት ቀን አለን አለን ይሏትና ይጠፉባታል፤ ሁል ጊዜ የጋለሞታ አይነት ሥርዓት እንዲኖራት ያደርጓታል፡፡ አንድ ወቅት ላይ የተመዘገበውን ታሪክ እናንሣና እንይ የኛም ታሪክ ያንድ ዘመን ማስታዎሻ እንደሚሆን እርግጠኞች ነን፡፡
በእናቱ ማኅፀን ውስጥ እንዲኖር የተፈቀደለትን ጊዜ ጨርሶ አንድ ሕጻን ወደ ዓለም እንዲመጣ ወደ እናቱ ሔዋናዊ መልእክት መጣ፤ ማለትም ሁላችንንም ወደ ዓለም ስንመጣ የቀደመን ምጥ በእናቱ ላይ የተፈጥሮ ሕጉን ጠብቆ መጣ፡፡ ዓለምን የተቀላቀልንበት ጉዞ የሚጀምረው በእናቶቻችን ምጥ ነው፤ ጉዟችን የሚያበቃው ደግሞ ከሞት ጋር በምናደርገው ትግል በሚፈጠር ምጥ ነው፡፡ በምጥ ጀምረን በምጥ እንጨርሳታለን፤ ዓለም እንዲህ ናት፡፡
 ታዲያ የዛሬው ባለታሪካችንም ሁላችንም በመጣንበት መንገድ ሊመጣ ግድ ነውና እናቱን አስጨንቆ ወደ ዓለም ሊመጣ ሲቃረብ የሴቲቱን ጭንቅ ብርቱ ያደረገባት ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁ? ሴቲቱ ብቻዋን የምትኖር ሴት ነበረች፤ ከጎኗ ሆኖ ጭንቀቷን ሊጋራት የሚችል አንድም ዘመድ የላትም፤ መከራን ለብቻ መሸከም ከባድ ያደርገዋል፡፡ ለነገሩ በሰው ሰውኛው ማለታችን ነው እንጂ ሰው ቢኖርስ ምን ያደርጋል፤ በዘመድ የከበሩ፣ በእውቀት የነጠሩ፣ በሀብት የበለጠጉ ብዙዎች ሲሞቱ እናውቅ የለ፤ ይህች ሴት ግን ምንም እንኳን የሚታይ ምድራዊ ዘመድ ባይኖራትም እግዚአብሔር ከሰማይ ዘመድ ላከላት፡፡
ሚካኤልና ገብርኤል የሚወለደውን ሕጻን