አሥሩ
የማሕሌት ደረጃዎች
ስለቅኔ ማኅሌት ባለፈው ተነጋግረን አሥሩን የማኅሌት ደረጃዎች ለዛሬ ልንነጋገር ቀጠሮ ይዘን ነበር የተለያየነው ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ እንዲህ እንቀጥላለን፡፡
የብሉይ ኪዳኑ ቤተ መቅደስ ላይ በመዝሙር እንዲያገለግል የተፈቀደለት ንጉሡ ዳዊት ነበር፤ የሚገርመው ነገር ለዚህ አገልግሎት ከተመደቡትና ቅብዓ ክሕነት ተቀብተው ከከበሩት ከሌዋውያን ይልቅ ዘፀ 40÷12 ነገዱና ሕዝቡ ከካሕናት ልዩ የነበረው እርሱ ለዚህ የተመደበ ነበር፡፡ በሃያ አራቱም ሰዓት ተመድበው ያለማቋረጥ ከሚያገለግሉ ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት መዘምራን ጋር እንዳንዱ በመሆን አሥር አውታር ባለው በገና በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ምስጋናን ያቀርብ ነበር፡፡
ዛሬም
በሐዲስ
ኪዳኑ
ቤተ
መቅደስ
ለዚህ
አገልግሎት
የተመረጠው
ያሬድ
ምንም
እንኳን
እንደ
ጥንቱ
በነገድ
የተከፋፈለ
አገልግሎት
ያላት
ቤተ
መቅደስ
ባትሆንም
በትምህርት
ተቀባይነት
ከሱ
የሚሻሉ
ሌሎች
ብዙ
ደቀ
መዛሙርት
እያሉ
ምንም
ከማያውቁ
እረኞች
እንዳንዱ
የሆነውን
ያሬድን
እግዚአብሔር
ለማኅሌታዊነት
መረጠው፡፡
እንደ
ንጉሡ
ቅዱስ
ዳዊት
ሁሉ
ከልቡ
የሚያፈልቃቸውን
የመዝሙር
ቃላት
አሥር
ምልክት
አውጥቶላቸው
አሥር
ደረጃ
ባለው
ማኅሌት
ያቀርባቸዋል፡፡
እያንዳንዳቸውን በዝርዝር ለማየት ከቅኝት እንጀምራለን፡-
1.
ቅኝት:-
ማለት
በቅኔ
ማኅሌት
የሚዜመውን
የእለቱን
ቃለ
እግዚአብሔር
ሊቃውንቱ
ሁሉ
በጋራ
ከማዜማቸው
በፊት
ከሊቃውንቱ
አንዱ
የተፈቀደለት
ሊቅ
የእለቱን
ቀለም
እንዲቃኘው
ይጋበዛል
የሚቃኘው
ሊቅ
አንድ
ጊዜ
ብቻውን
ከዘለቀው
በኋላ
ሌሎች
መምህራን
ተከትለው
ይሉታል፡፡በዚህ
ሂደት
ቤተክርስቲያናችን
ሁለት
ምሥጢራዊ
መልዕክቶችን
ታስተላልፍበታለች።
1.1 ኃጢአት ወደ ዓለም የገባበትን መንገድ፡- ኃጢአት ወደ ዓለም የገባው በአንድ አዳም ቅኝት በልጆቹ ተቀባይነት ነው፡፡ በገነት ማኅሌት ውስጥ መምህሩ ሰይጣን እንዳስተማረው የሁላችን አባት አዳም በአብራኩ ውስጥ ያለን ፣ ነገር ግን ገና ያልተወለድን ልጆቹ እስክንሰማው እና መቀበል እንድንችል አድርጎ ቅኝቱን አዜመው፡፡ እኛም ተቀብለነው እሱ በቁም ዜማ ያዜመውን እኛ ልጆቹ ጸናጽልና መቋሚያ ጨምረንበት ማለትም እሱ በስህተት የሠራውን እኛ የድፍረት ኃጢአት ጨምረንበት እየተስማማን ስናዜመው ቆየን፡፡