ሙሴና ኤልያስ በደብረ ታቦር
ደብረ ታቦር ከደብረ ሲና የሚበልጠውን ምሥጢር ያየንበት ተራራ ነው፤ በደብረ ሲና በሁለቱ
ጽላት ላይ የተጻፉ ቃላትን ተቀብለናል፤ በደብር ታቦር ግን አካላዊ ቃል ተገልጦ ታየልን፤ በደብረ ሲና ሙሴ ብቻውን ቆሞ ነበር በደብረ
ታቦር ግን ነቢያት ከሐዋርያት አንድ ሆነው ተስማምተው ክርስቶስን መካከል አድርገው ታዩ፡፡ እነዚህ ሁለቱን ከነቢያት ለይቶ ለምን
ይጠራቸዋል፤ ከነሱ በላይ የሚጠራቸው አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉ አይደለምን! ሙሴና ኤልያስ ለምን ለዚህ ምሥጢር የተለዩ ሆኑ?
ቅዱስ ወንጌል ‹‹ወናሁ አስተርአዩ ሙሴ ወኤልያስ እንዘ ይትናገሩ ምስሌሁ፤ እነሆ ሙሴና
ኤልያስ ከእርሱ ጋር እየተነጋገሩ ታዩ›› ማቴ 17÷4 ብሎ በስም የጠራቸው እነዚህ ነቢያት ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ሁሉ የሚያመሳስላቸው
ታሪክ ያላቸው ነቢያት ናቸው፤