ጠላቶቻችን ሆይ!
በሥጋ ወንድሞቻችን በወንጌል በኩል ግን ጠላቶቻችን ከሆኑ ሰዎች ጋር ለመኖር ልምድ ያለው እንደ ኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማንም በዓለም ላይ ይኖራል ብየ አላስብም፡፡ አባቶቻችን ጊዜ ቢያጋጥማቸው ሥልጣን ቢደላደልላቸው
እንደ መንግሥት ያስገብሩ ይሆናል እንጅ ማንንም በሃይማኖት ምክንያት በደል አያደርሱም ነበር በእርግጥ ማዕከላዊው የኢትዮጵያ መንግሥት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቅብዓ መንግሥት አክብራ የሾመችው እንደ መሆኑ ክርስቲያናዊ መንግሥት በመሆኑ ምክንያት የተለያዩ የጎሣ መሪዎች በተለያዩ ጊዜያት ክርስቲያን የመሆን አዝማሚያ ይታይባቸው ነበር ነገር
ግን በራሳቸው ፈቃድ እንጅ ማንም አስገድዶ ክርስቲያን አላደረጋቸውም፡፡
ምን አልባትም በሃይማኖት ምክንያት ቁጥጥር ተደርጎ ከሆነ በኢትዮጵያ ታሪክ እንደ አባ ጅፋር ባሉ
አክራሪ እስላሞች የተደረገው ነው እሚሆነው፡፡ አባ ጅፋር ጅማን በሙሉ እስላም ለማድረግ ቋንቋዋንም አረበኛ ለማድረግ ይሠሩ ነበር
ይባላል ያንጊዜ ዓጼ ምኒልክ ሰምተው ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደ ጻፉላቸው ጳውሎስ ኞኞ ጽፏል፡፡ የሐረር ሡልጣኖችም ከዓጼ ምኒልክ
ጋር ጦርነት የመክፈታቸው ምክንያት እስላም በመሆናቸው ሳይሆን ማዕከላዊው መንግሥትም እስላም ካልሆነ አንገብርም በማለታቸው እንደሆነ
ተጽፏል፡፡ እንዲያውም ግብር እንዲያስገቡ ወታደሮች ሲላኩ የእስላም ቆብና ጀለብያ ለዓጼ ምኒልክ ልከውላቸዋል ይባላል፡፡
ይህ በመሆኑ ምክንያት ካልሆነ ከጠላት ጋር ሀሳቡን አክብሮ በመኖር ከእኛ ጋር የሚተካከል ታሪክ ያለው
ሰው ማነው? ከዛሬ በቀር በወንጌል ካልሆነ በሥጋ ጠላት ኖሮብን አያውቅም ነበር፤ ዛሬ ግን በወንጌል ብቻ ሳይሆን በሥጋም ጠላቶቻችን
በዙ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለ እግዚአብሔር መንግሥት መከራን እየተቀበሉ ነው፡፡
ሲገድሉንም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከነገሥታቱ ጋር ሆና እንደ በደለቻቸው ሲናገሩ ይሰማል፤ ነገር
ግን ታሪክ ባለማወቃቸው ይስታሉ እንጅ ታሪካችን እንደዚያ አያሳይም፡፡
እስላም ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ እኛኮ በመንግሥት ደረጃ ተዋቅረናል፤ የኢትዮጵያ ክርስትና እንደ ሌሎቹ ሀገራት በሕዝባዊ ቤት የተጀመረ
አይደለም በነገሥታት ቤተ መንግሥት ተጀምሮ እየተስፋፋ የመጣ ነው እንጅ፡፡ ያንጊዜ ነገሥታቱ ያለ ምክረ ካህን በኢትዮጵያ ላይ እንዲቀመጡ
ሚፈቅድላቸው ይመስላቸዋል? አጼ ገላውዴዎስ የፖርቹጋልን ወታደሮች አስወጥተው የሰደዷቸው እኮ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ስላልፈቀዱ
ነው እንጅ የቤተ መንግሥቱ መሳፍንት ጋር ተማክረው አልነበረም፡፡
አናሲሞስ ነሲቡንስ በነጻነት እንዲንቀሳቀስ ያደረገው ማን ነው? በወቅቱ ከዓጼ ምኒልክ የፈቃድ ደብዳቤ
እንዲሰጠው እና ወደ ወለጋ ሂዶ ወንጌል እንዲሰብክ መጽሐፍ ቅዱስን በኦሮምኛ አሳትሞ እንዲያሰራጭ ያደረገው ማነው? ብፁዕ አቡነ
ማቴዎስ ናቸው፡፡ ያ ባይሆን ኖሮ ፕሮቴስታንት በኢትዮጵያ መኖሩ ያጠራጥር ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ለክፉዎችም ለዳጋጎችም
ነፍስን አሳልፎ መስጠትን እንጅ በክፉ ዓለም ውስጥ ከደጋጎቹ ጋር ብቻ መኖርን አታስተምርም፡፡
Ø ጠላቶቻችን ሆይ! ከአባታችሁ ሰይጣን የተማራችሁትን መግደል ማስቆም ባንችልም እናንተም ሃይማኖታችንን ማስቆም አትችሉም፡፡
Ø ጠላቶቻችን ሆይ! ስለክርስቶስ መሞትን አባቶቻችን ሐዋርያት አስተምረውናል፤ አምኖ መሞት እንጅ ሃይማኖትን ክዶ በሕይወት መኖር በእኛ
ዘንድ ሕይወት አይደለም፡፡
Ø ጠላቶቻችን ሆይ! ስታሳድዱን ያንጊዜ ዝም የምንለው ከፊታችን ያለው ክርስቶስ ‹‹ሲነቅፏችሁና ሲያሳድዷችሁ ደስ ይበላችሁ በሰማይ ዋጋችሁ
ታላቅ ነውና›› ማቴ 5፥10 እያለ ስለሚያጽናናን ነው፡፡
Ø ጠላቶቻን ሆይ! ቤታችንን ንብረታችንን ስታቃጥሉ ዝም ያልነው ‹‹በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና
ብሎ ያስተማረን መለኮታዊ ቃል ስላለን እሱ ትዝ እያለን ነው፡፡
Ø ጠላቶቻችን ሆይ! እናንተ መንገድ ላይ ወጥታችሁ ስትዘፍኑ
እኛ ኀዘን የተቀመጥነው፤ እናንተ መንገድ ለመዝጋት ስትሰለፉ እኛ ለምኅላ የቆምነው ‹‹ዛሬ የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው መጽናናትን ያገኛሉና››
ስለሚል ነው፡፡ ኃጢአት ሠርቶ ከመደሰት ስለ ክርስቶስ መከራ እየተቀበሉ ማዘን ይበልጣልና፡፡
Ø የአብርሃም አምላክ ካራንን ልቀቁ ሲል
የተሻለች ከነዓንን ለአብርሃም አዘጋጅቶ ነው፤ አትጠራጠሩ እናንተ ሣራን ለራሳችሁ ለማድረግ ስትሮጡ እግዚአብሔር አጋርን ሳይቀር
ከእጃችሁ ነጥቆ ለአብርሃም ያደርጋታል፡፡
Ø እናንት ሰነፎች ሆይ! ኢትዮጵያ እንደ
ሣራ ናት፤ የነቢይ ሚስት ናትና ንጉሥ አያገባትም፡፡ ውበቷ አስክሯችሁ ደም ግባቷ አስቷችሁ ክፉ ባታደርጉ መልካም ነው፤ ኢትዮጵያ
የንጉሡ ናት፡፡ በእናንተ ፊት አንገቱን የደፋው አብርሃም ካልጸለየላችሁ የማትድኑበት ወራት ይመጣልና አብዝታችሁ አትበድሉ፡፡
No comments:
Post a Comment