>

Tuesday, 13 September 2016



አዲስነገርየለም
አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ሚመጣልን በተስፋ ሰምተናል፤ ክርስቶስ በዚህ ምድር በነበረ ጊዜ አዲስ ያደረገው የሰውን ሕይወት እንጅ ምድርን አዲስ ማድረግ አልነበረም- የመምጣቱ  ዓላማ፡፡ ኃጢአት ያስረጀውን ዓለም ያለ ኃጢአት ተወልዶ በኃጢአት ያለውን የሰውን ልጅ ደግሞ በመስቀል ኃጢአትን አስወግዶ የሰውን ልጅ አዲስ አደረገው፡፡
አሁን ግን አዲስ ነገር የለም ያልኩት ሰው ወደ ጥንት ክፋቱ የተመለሰ ስለመሰለኝ ነው፤ እርግጥ ነው ዛሬ ያለንበት ቀን ባለፈው ዓመት በመምጣቱ ደስ ብሎን የተቀበልነውን ዓመት 2008ን አለቀብንና አሮጌ ብለን በአዲስ ልንተካው እየተዘጋጀን ያለንበት ወቅት ነው፡፡ ነገር ግን ዓመታት አዲስ የሚሆኑት ሰው በሕይወቱ አዲስ ነገር ሲያገኝ ብቻ ነው፡፡
ኃጢአትን በማይፀየፍ ሕይወት ውስጥ ሆኖ አዲስ ነገር እንዴት ይኖራል፤መጽሐፍ ‹‹ከፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም›› ብሎ የተናገረው ለምን ይመስላችኋል ያኔ በወቅቱ የሰውን ልጅ ኑሮውን አዲስ ማድረግ የሚችል ምንም አይነት ነገር እንደ ሌለ የሚያሳይ እኮ ነው፡፡
ክርስቶስ ሲመጣ ግን አዲስ ዘመን፣ አዲስ መሥዋዕት፣ አዲስ መንገድ፣ አዲ ስ ሰማይ አዲስ ምድር፣ አዲስ ትምህርት አዲስተስፋ ከሁሉም ነገር በላይ ደግሞ አዲስ ሰው ተፈጠረ፡፡ ሐዋርያት ‹‹ልበስዎ ለሐዲስ ብእሲ፤ አዲሱን ሰው ልበሱት›› ቆላ 3÷10 ብለው መናገር ጀመሩ አዲስ ሆነዋልና በአዲስ ቋንቋ ተናገሩ አዲሱ ኪዳን ተጀምሯልና ሰውን ሁሉ አዲስ የሚያደርገው ሥልጣነ ክህነት ባለቤት ሆኑ፤
አዲስነታቸው አዲስ ነገርን እያስገኘላቸው ለብዙ ሰዎች መዳን ምክንያት የሆነ ክርስቲያናዊ ሕይወት ነበራቸው፤ ክርስቶስ ወደ ዓለም ሲመጣ በአዲስ ልደት እንደ ሆነ የታወቀነው፤ በምድራችን ላይ ያለ አባት የተወለደ ኅጻን ያለ ወንድ ዘር የወለደች እና ከወለደችም በኋላ በድንግልና ጸንታ የኖረች ሴት ያን ጊዜ ብቻ ካልሆነ ከዚያ በፊት የት እናገኛለን፡፡ በዚያውም ላይ ቅዱስ መጽሐፍ የሚነግረን  ያለ ሴት ሴትን ማስገኘት የሚችል ወንድ መኖሩን ነው እንጅ ያለ ወንድ ወንድን ማስገኘት የምትችል ሴት መኖሯን አይደለም፤ ዘፍ 2÷21 አሁን ግን ያ ሕግ ተሸሮ ያለ ወንድ ወንድን የምታስገኝ ሴት ድንግለeል ማርያም በምድራችን ተገኘች፡፡
በዚህ አዲስ ልደት የመጣው ክርስቶስ ሥራውን የጀመረው በቤተ መቅደስ በር ላይ የነበረውን አረጋዊ ስምዖንን አዲስ በማድረግ ነው፤ ዓላማውም ይህ ነበርና-ሰውን አዲስ ማድረግ፡፡
ሰው አዲስ ከሆነ ምን አሮጌ ነገር ሊኖር ይችላል፤ አዲስነታችን ሁሉን ነገር አዲስ ሊያደርገው እንደሚችል አታወቁም? አዲስ ልብ አዲስ መንፈስ ሊኖረን ይገባል፤ ከሁሉም ሰው ጋር በፍቅር የምንኖርበት፣በጨለማ ውስጥ ላሉት ብርሃን የምንሆንበት፣ያዘኑት የምናጽናናበት፣ስብራትን የምንጠግንበት፣ድካምን የምናበረታበት አዲስ ልብ ሊኖረን ይገባል፡፡
አዲስ ልብ ሳይኖረን ምን አዲስ ነገረeር ሊኖር ይችላል፤ እመኑኝ አዲስ ነገር ሊኖር የሚችለው አዲስ ልብ ሲኖረን ብቻነው፤ አዲስ ልብስ ገላን እንደ ማያጠራው ሁሉ አዲስ ዘመንም ሰውን  አዲስ ሊያደርገው አይችልም፤ የሰው አዲስነት ዘመኑን፣ ምድሩን፣ ነፋሱን፣ ውኃውን አዲስያደርገዋል፡፡
በሌላው ዓለም እንዳየነው ብዙ አንገት የሚያስደፉ ነገሮችን እየተመለከትን ምድር በሰው ደም እየታጠበች እናቶች ያለ ልጅ ሲቀሩ እያየን ይቅር ሳንባባል አንዳችን በአንዳችን ላይ ሰይፍ እየተማዘዝን የመዘዝነውን ሰይፍ ወደ ሰገባው ሳንመልሰው ምን አዲስ ነገር ሊኖር ይችላል፤ እውነት ነው እምላችሁ የሰው ደም የፈሰሰባት ምድር ራሷ እንደምትሞት ታውቃላችሁ፤ ሙት ባሕር የሚባል ሕይወት የሌለው ውኃ በዓለማችን እንዲኖር ምክንያቱ ምን እንደ ሆነ አታውቁም እንዴ፤ ወንድሙ ቃኤል በገደለው ጊዜ የጻድቁ የአቤል ደም የተጨመረበት ስለሆነ እኮ ነው፤
ደም እያፈሰስን ምድሩን ባሕሩን ነፋሱን ሌላውንም ነገር ለምን እንገለዋለን በሞ ተች ምድር ላይ ዘርተን በሞተ ውኃ አብቅለን የሞተ ዓየር ስበን እንዴት በሕይወት ልንኖር እንችላለን መጨረሻችን መተላለቅ ሳይሆን ነገሮችን ሁሉ ምክንያት ሳንሰጥ በይቅርታ ምድርን አዲስ ልናደርጋት ይገባናል፡፡ ሔሮድስም ሔሮድያዳም ወለተሔሮድያዳም በዮሐንስ ሞት ተሳትፈዋልና በንስሐ እስካልተመለሱ ድረስ እግዚአብሔር የሔሮድስን ቤት አንድ ቀን ያጠፋታል፡፡
ነገሥታት ለእግዚአብሔር የተገዙ እንደ ሆነ ከዙፋናቸው ዘር አይታጣም መዝ 131÷11 ይህ ካልሆነ ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን ለጨካኝ መንግሥት ሰጥቶ ዝም የሚል አምላክ አይደለምና ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ሊመለስ ይገባዋል፤ የዳዊት መንግሥት ለምን ተቀደደች? 1ነገ 12÷16፣ ግብጽ ንጉሷን አጥታ ለምን ባዶዋን ቀረች? ዘፀ14÷28 በጭካኔ ሕዝቡን የሚገዙ ነገሥታትን ማጥፋት የእግዚአብሔር ሥራነው፤ እኛ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ እግዚአብሔርም ወደ እኛ ይመለሳል፡፡
አሁንም እንዘፍናለን፤ አሁንም እናመነዝራለን፤ አሁንም ያለ ልክ እንበላለን እንጠጣለን ማነው በሞት ፍርሃት ያልተከበበ፤ ማነው በኑሮ ክብደት ያልተንገዳገደ፤ ማነው የኃዘን የለቅሶ ድምጽ ሳይሰማ የዋለ፤ በከተሞቻን ሁሉ ሞት ና ግድያ አለ፤ በቀኖቻችን ሁሉ እነዚህ ነገሮች ነበሩ፤ አብረውን ተሻግረው ይሆን፡፡ በአሮጌ ልብስ ላይ አዲስ መጣፊያ መጨምር በአሮጌም አቀማዳ አዲስ የወይን ጠጅ መሾም ምን ያደርጋል፤ ልብሱም ይቀደዳል ወይኑም ይደፋል
እግዚአብሔር ዘመኑን ይባርክልን ያለፈው ክፉ ዘመን ደግሞ ወደ ዚህኛው አይምጣብን፡፡

Thursday, 18 August 2016



ሙሴና ኤልያስ በደብረ ታቦር
ደብረ ታቦር ከደብረ ሲና የሚበልጠውን ምሥጢር ያየንበት ተራራ ነው፤ በደብረ ሲና በሁለቱ ጽላት ላይ የተጻፉ ቃላትን ተቀብለናል፤ በደብር ታቦር ግን አካላዊ ቃል ተገልጦ ታየልን፤ በደብረ ሲና ሙሴ ብቻውን ቆሞ ነበር በደብረ ታቦር ግን ነቢያት ከሐዋርያት አንድ ሆነው ተስማምተው ክርስቶስን መካከል አድርገው ታዩ፡፡ እነዚህ ሁለቱን ከነቢያት ለይቶ ለምን ይጠራቸዋል፤ ከነሱ በላይ የሚጠራቸው አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉ አይደለምን! ሙሴና ኤልያስ ለምን ለዚህ ምሥጢር የተለዩ ሆኑ?
ቅዱስ ወንጌል ‹‹ወናሁ አስተርአዩ ሙሴ ወኤልያስ እንዘ ይትናገሩ ምስሌሁ፤ እነሆ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር እየተነጋገሩ ታዩ›› ማቴ 17÷4 ብሎ በስም የጠራቸው እነዚህ ነቢያት ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ሁሉ የሚያመሳስላቸው ታሪክ ያላቸው ነቢያት ናቸው፤

Wednesday, 10 August 2016

ሱባኤ



ሱባኤ
·        ---- --------------- የሱባኤ ጥቅሙ ምንድነው?
·      , ------------   ------እመቤታችን የሞተችው በጥር ከሆነ ሐዋርያት እስከ ነሐሴ ሱባኤ ያልገቡት ለምነድነው?
·         ---------------ትንሣኤዋ በሦስተኛው ሱባኤ ተገለጠላቸው ሱባኤውን ያልጨረሱት ለምንድነው?
--------እነዚህን እና ሌሎችን ጥያቄዎችን በዚህ ጽሑፍ ለመመለስ እንሞክራለን
ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር እንዲደረግልን ስንሻ ሱባኤ መግባት በአባቶቻችን ሕይወት የተማርነው የጥያቄ ማቅረቢያ መንገድ ነው፤ በሱባኤ ምሥጢር ይገለጣል፤ በሱባኤ በረከት ይገኛል፤ በሱባኤ ዕጣ ፋንታን ማስተካከል ይቻላል፤ ሁሉም በጎ ነገሮች የሱባኤ ውጤቶች ናቸው፤ የሔዋን መፈጠር በሱባኤ ነው የእስራኤል ከፋርስ ባቢሎን መውጣት በሱባኤ ነው፤ የክርስቶስ ልደት በአበው ሱባኤ ነው፤ የሰው ልጆች ከሲኦል መውጣት በሱባኤ ነው፤ በመጨረሻም የታላቁ ዓለም የመንግሥተ ሰማያት መምጣት በሱባኤ ነው፤

Sunday, 24 July 2016

ተፈጸመኩሉ




በእርግጥይሄንቃልየሕይወትፍጻሜ ሆኖ ነው የምናውቀው፤ ክርስቶስ በመስቀልላይ ራሱንሰጠናፍቅርፍጻሜውንሲያገኝ ‹‹ተፈጸመኩሉ›› አለሁሉምነገርበፍቅርይፈጸማልናማለትፍቅርሁሉንነገርፍጹምያደርጋልና፡፡
ድሮድሮአንድነገርያልቃልእንጅሁሉነገርአለቀአይባልምነበር፤ በገሊላዊቷታናሽመንደርበቃናውስጥያለቀውወይኑብቻነበርእንጂሌላነገርእንዳለቀአልተጻፈልንም፤ አባቶቻችንሐዋርያትከአምስትእንጀራእናከጥቂትዓሣበቀርየለንምብለዋልእንጅምንምእንደሌላቸውአልሰማንምማቴ 14÷17ከኤልያስዘመንየሚከፋየረሀብዘመንየትይገኛል፤ነገርግንከሰራፕታዋሴትቤትከራሷአልፎለመንገደኛውለኤልያስየሚተርፍበረከትእንደነበረተጽፏል 1ነገ 17÷12 ያዕቆብንበእርጅናውወራትእንዲሰደድያደረገውንከነዓንንምድረበዳአድርጎሕዝቦቿንያስመነነውንታላቁንረሀብየምትረሱትአይመስለኝምዘፍ. 47÷4 ብዙሕዝብእንጀራላለውአንድንጉሥእንዲገዛያደረገከባድየረሀብዘመንነበረነገርግንምግብከብዙሀገሮችጠፍቷልእንጅበግብጽእግዚአብሔርበዮሴፍበኩልየሰበሰበውበረከትእንደነበረየታወቀነው፡፡
ታዲያእንዲህከሆነ ‹‹ተፈጸመኩሉ›› ብለንየሁሉንነገርማለቅየምናረጋግጠውምንሲሆንነውያልንእንደሆነቀንያለቀብንእንደሆነብቻነውቀንሲያልቅሁሉነገርያልቃል፤ ሌላውንነገርሁሉበቀንይሠሩታልቀንቢያልቅበምንይሠሩታል?

Monday, 4 July 2016



አሮን ለራሱ ሙሴ ለመቅደሱ




Ø  የቤተ መቅደስ አገልግሎት ራስን በመካድ ይጀምራል፤ ራሱን ያልካደ አገልጋይ እግዚአብሔርን ማገልገል የማይችል የራሱ አገልጋይ ነው፡፡ ለአንድ አገልጋይ ወደ አገልግሎት ከመግባት በፊት
Ø  ጥዎተ ርእስ
Ø  ጋህ
Ø  ሎት
Ø  እግሥት
እነነዚህ አምስት ነገሮች ያልተሟሉለት አገልጋይ ውኃ በሌለበት ምንጭ ይመሰላል፤ዝናም ያልቋጠረ ደመና ምድሩን ሲዞር ቢውል ምን ያደርጋል ከማኅፀኑ አውጥቶ ምድርን የሚያረካበት አንዳች ጠብ የሚል ውኃን አልቋጠረምና፡፡
ከእነዚህ ነገሮች የተለየ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋይም እንዲሁ ነው፤ ያለጸሎት እንዴት የሚያስተምረው ትምህርት በምእመናን ልቡና ተዘርቶ ይበቅልለታል፤ ያለ ትእግሥት በሃይማኖት የሚመጣበትን ፈተና እንዴት ድል መንሳት ይችላል? ያለ ትጋት መንጋውን እንዴት መጠበቅ መመገብ ይችላል? ራስን ሳይሰጡ እንደምን አድርጎ ምእመናንን ያለጥቅም መውደድ ይቻላል? ያለ መሠረታዊ እውቀትስ ወንጌልን እንዴት ይኖሩታል?
የዘራነው አልበቅል አለ የተከልነው አልጸድቅ አለ ወይን ዘርተን እሾህ፣ ስንዴ ዘርተን እንክርዳድ እየሆነብን ነው፤ እየጸለይን እንዝራው እየዘመርን እንሰበስበዋለን፤ አባቶቻችን ለሥራ ሲነሡ አስቀድመው ጾምና ጸሎትን ይይዙ እንደነበረ መጽሐፍ ምስክር ነው ሥራ 13÷4 ለወንጌል አገልግሎት ከመጠራት በላይ የሆነ ምንም አይነት ሥራ የለም፤ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነውና፡፡ ለዚህ ሥራ ራሳቸውን ለሰጡ ሰዎች መንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ ቀጥሎ በሚደረግ ተዓምር ሥራቸውን ያከናውናላቸዋል ማር 16÷17 የዓይናችን ብሌን ከጸሐይ ብርሃን ጋር ካልተዋሐደ የዚህን ዓለም ብርሃን ማየት አንችልም የልባችንም ዓይን ከመንፈስ ቅዱስ ጸዳል ጋር ካልተዋሐደ እግዚአብሔርን ማየት አንችልም አባቶቻችን ለሕዝቡ የሚሆነውን ፀሐይ የሚያወጡ ንጋቶች ናቸው፤ ፀሐይን እናይባቸዋለን፡፡
የሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ለሕዝቡ ካልጠቀመ ምን ያደርጋል፤ ስድት መቶ ሺህ ሕዝብ አብነት የሚያደርገው ሰው አጥቶ እየተጨነቀ የሙሴ ወደ ተራራው መውጣት ምን ጥቅም አለው፤ አሮን ራሱን ያልካደ አገልጋይ ነው ለመቅደሱ ሥራ እስከ ልጅ ልጆቹ ድረስ የተለየ የእግዚአብሔር ካህን እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም ዘፀ 40÷12 የበፍታ ኤፉዱን ሲለብስ ያምርበታል፤ በወርቅ ማዕጠንቱ ድውያን ይፈወሱለታል፤ በሚሠዋው መሥዋዕት የኃጢአት ሥርየት ይሰጥለታል እግዚአብሔር በጠላት ፊት ሊናገርበት አንደበቱን ባርኮለታል ከሙሴ ይልቅ ተናግሮ እንዲያሳምን ጥሩ አንደበት ተሰጥቶታል፤ ግን ምን ያደርጋል አሮን ሕዝቡን ግብጻዊነት ሲያጠቃው እያየ ያቀረቡለትን የጆሯቸውን ጌጥ እንደ ግብጽ ልማድ የጥጃ ምስል አድርጎ ሠርቶ ለሕዝቡ እንቅፋትን ፈጥሮባቸዋል፤
አሮን ከሕዝቡ የሚመጣበትን መከራ እንዳይቀበል ትእግሥት አጣ እውነቱን እንዳይናገር ራሱን አልካደም ራሱን ያልካደ አገልጋይ እንደምን አድርጎ እውነትን በምትጠላ ዓለም ፊት እውነትን መመስከር ይችላል በዓለም ላይ እውነትን ከመናገር በላይ ምን የሚያስፈራ ነገር አለ፤ ዓለምም እንደ እውነት የምትጠላው ምንም አይነት ነገር የላትም፤ ስለዚህ ራሳቸውን ላልካዱ አገልጋዮች ዓለም ክንደ ብርቱ ናት፡፡ አሮን በዚያ አንደበቱ ለሕዝቡ እውነት ቢናገር ኖሮ ተራራው ላይ ካለው ከሙሴ ይልቅ የተሻለ ጽድቅ በተገኘበት ነበር፤ በእርግጥ ከተራራው ግርጌ ላሉ ሰዎች ይሄ ነገር ከባድ መሆኑን አውቃለሁ፤
ከተራራው ግርጌ ያለ ሕዝብስ እንዴት ለእግዚአብሔር ሕግ ሊገዛ ይችላል፤ የእውቀት የንጽሕና የቅድስና የምንኩስና ተራራን መውጣት የቻሉ እነ ሙሴ ካልደረሱለት ከተራራው እግር ሥር ሁከት ዘፈን ጭፈራ መቸም አይወገድም፤ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ይመለስ ግብጻዊነት ይጥፋ አምልኮተ እግዚአብሔር ይስፋ ካላችሁ አሮንን ተውትና ሙሴን ከተራራው ላይ እንዲልከው ጸልዩ የሚገሥጸው ሙሴ ካልመጣ የአሮን ዝምታ አልጠቀመንም፤
አባቶቻችን እንደ ሙሴ ካልሆኑ ጣዖቱ አይሰበርም፤ ሕዝቡ ይቅርታ አያገኝም፤ የቃል ኪዳኑን ምድር አይወርስም፤ ተስፋው አይፈጸምም፤ ጉዞው አይቀጥልም፤ ጠላት አይሸነፍም፤ ስለዚህ ይህን እንደ ወይን ስካር ባለ ኑሮ ውስጥ የሚኖረውን ሕዝብ የሚያወጣ ሙሴ ከተራራው ሊወርድልን ይገባል፤ አሮን ዝም ባይል የጥጃው ምስል የወርቁ እንክብል ባልገዛንም ነበር፤ ግና ምን ይሆናል አሮን ለራሱ ክብር ሲል ሕዝቡን ከክብር አጎደለው፤ ሙሴ ስለመቅደሱ ሥርዓት ለመነጋገር ከእግዚአብሔር ጋር ቆሟል አሮን ለራሱ ሙሴ ለመቅደሱ ይተጋሉ፡፡ ዘፀ 32÷1-35   
በዚህ ዘመን ሊሾሙ የሚገባቸው አባቶችም እንደ ሙሴ ተራራው ላይ ወጥተው የሚዘገዩ እንደ አሮን ራሳቸውን የሚጠብቁ ሊሆኑ አይገባም፤ ሕዝቡ ጠንካራ መንፈሳዊ መሪ ከሌለው ከአርባ ቀን በላይ አይቆይም፤ ታሪክ ያበላሻል፤ እግዚአብሔርን የሚያስቀይም ሥራ ይሠራል፤ ስለዚህ አባቶቻችን ሕዝቡ የጠየቃቸውን አድርገው በሕይወት ከሚኖሩ ይልቅ ከፊት ቀድመው ‹‹የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ወደ እኔ ይምጣ›› ዘፀ 32÷26 ቢሉ ሁሉም ይከተላቸዋል፤
ወደ ፊት የሚሾሙልን አባቶችም ከተራራው ላይ ያለውን የእግዚአብሔር ትእዛዝ የሚነግሩን እንጅ ከግብጽ በወረስነው ክፉ ልማድ ስንጎዳ ዝም የሚሉን እንዳይሆኑ በታቦቱ የዓለምን ጣዖት የሚሰብሩ ለምድሩ ሳይሆን ለሰማዩ መንግሥት የሚሠሩ እንዲሆኑ ሁላችንም ልንጸልይ ይገባናል፡፡
አባቶቻችን ሆይ! አርባ ቀንም ታሪክ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ እናንተን በመንጋው ላይሾሟችኋልና ሕዝቡን ከሙሴ በተረከባችሁት መንፈስ ልትመሩት ይገባል፤ እናምናለን እናንተ በሙሴ መንገድ ከተጓዛችሁ የአባቶቻችን አምላ ከእናንተ ጋር እንደሚሠራ፡፡ በአበው መንፈስ ካልሆነ ግን ሙሴ አርባ ዓመት የመራውን ሕዝብ ከአርባ ቀን በላይ እድሜ እንዳይኖረውና የእግዚአብሔርም ቁጣ በሕዝቡ ላይ እንዲነድ ታደርጉታላችሁ፡፡



Saturday, 18 June 2016

አዲሱን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር


እስራኤል የሚያከብሯቸው ዘጠኝ ያክል በዓላት ያሏቸው ሲሆን በተለየ ሁኔታ ሦስት ዐበይት በዓላት አሉ፤ እነርሱም፡- በዓለ መፀለት፣ በዓለ ፍሥሕ እና በዓለ ሰዊት፤ ናቸው ዛሬ ማየት ምፈልገው በዓለ ሰዊትን ነው፤ይህ በዓል ፋሲካን ካከበሩ በኋላ በሃምሳኛው ቀን እንዲያከብሩት የታዘዘ በዓል ነው ‹‹ከሰንበት ማግስት ፍፁም ሰባት ሱባዔ ቁጠሩ እስከ መጨረሻ ሰባተኛ ሰንበት ማግሥት ድረስ አምሳ ቀን ቁጠሩ አዲሱንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ›› ዘሌ 23÷16 አዲስ መሥዋዕት ያቀርቡባት ዘንድ የተዘጋጀች አዲስ ቀን ናት ባለፈው በዓለ ፍሥሕን ሲያከብሩ ‹‹እንጀራውንም የተጠበሰውንም እሸት ለምለሙንም እሸት የአምላካችሁን መሥዋዕት እስከምታቀርቡበት እስከዚህ ቀን ድረስ አትብሉ›› ዘሌ 23÷14 ተብለው መታዘዛቸውን እናስታውሳለን፡፡
ከስሙም እንደምንረዳው በዓለ ሰዊት ማለት የእሸት በዓል ማለት ነው፤ አዲሱ እህል ሲደርስ የምድሩን ፍሬ ቀዳምያት ለእግዚአብሔር የሚያስረክቡበት ቀን ነው ዓለም የሚድነው በቀዳማዊ ቃል ነውና ቀዳምያቱ ለእግዚአብሔር ይገባ ነበር፤ ቀዳማዊ ቃል ሥጋን ለብሶ እስኪመጣ እና ቀዳማዊ ቃል የተዋሐደውን ሥጋ መሥዋዕት አድርገን በፊቱ እስክናቀርብ ድረስ ሌላ ምን ይዘን ልንቀርብ እንችላለን፤

Thursday, 9 June 2016

እርገት

የዛሬው እርገት በሥጋ የተደረገ እርገት እንጅ እግዚአብሔር በባሕርዩ ከዚህ ያለ ከዚያ የሌለ ሆኖ ከዚህ ወደዚያ ሄደ ማለታችን አይደለም፤ ሰው በሆነ ጊዜ ከሰማየ ሰማያት ወረደ ማለታችን ከዚህ የሌለ በዚያ ብቻ ያለ ነው ማለታችን ሳይሆን ምድራዊነትን ገንዘብ አደረገ ማለታችን እንደሆነ ሁሉ አሁንም ወደ ሰማይ ወጣ ስንል በሥጋ ግብር መናገራችን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በእርግጥ ልንረሳው እማይገባ ዋናው ነገር የሥጋ እርገት የቃል ርደት የተፈጸመው በማኅፀነ ማርያም መሆኑን ነው ለዚህ ነው ሊቁ አባ ሕርያቆስ እመቤታችንን ባመሰገነበት ድርሳኑ ‹‹ ምዕራግ እምድር እስከ ሰማይ፤ ከምድር ወደ ሰማይ መውጫ መሰላል ሆይ..›› ብሎ ማመስገኑ፡፡ ጌታችንም ከእርገት አስቀድሞ በመዋዕለ ስብከቱ ‹‹አልቦ ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ፤ ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም›› ዮሐ 3÷13 ብሎ ያስተማረው እርገት በማኅፀነ ማርያም ስለተፈፀመ ነው፡፡ ታዲያ እንዲህ ከሆነ የዛሬው እርገት ምንድነው? ብሎ የሚጠይቅ ቢኖር

Wednesday, 4 May 2016

ማዕዶት



ከትንሣኤ  በኋላ የምናሳልፈው ሳምንት በቤተ ክርስቲያናችን ስያሜ ማዕዶት ተብሎ ይጠራል፤ መሸጋገሪያ ማለት ነው፤ ሳይሻገሩ የተስፋይቱን ምድር መውረስ እንዴት ይቻላል! ያልተሻገረ ሕዝብ ባሪያ ነው ዘፀ 5÷2 ያልተሻገረ ሕዝብ እረፍት የለውም ዘፀ 5÷17 ያልተሻገረ ሕዝብ ከዓለም አስጨናቂነት የተነሣ ነፍሱ ተጨንቃ የእግዚአብሔርን ቃል እንዳይሰማ ታደርገዋለች ዘፀ 6÷9 ያልተሻገረ ሕዝብ ነፍሱን ከገዳየቹ እጅ ማዳን አይችልም፤ ከሞትም ጋር ተስማምቶ ይኖራል ዘጸ 1÷16 ያልተሻገረ ሕዝብ የሰው ከተማ ይገነባል ዘፀ 1÷11 ብቻ ያልተሻገረ ሕዝብ ነጻነቱን፣ ክብሩን፣ ማንነቱን፣ ሀገሩን፣ ሃይማኖቱን እና ሌሎችንም አጥቶ ከተስፋ ርቆ ይኖራል፡፡
ይህ ሁሉ ችግር ወደ ነበረበት ሕዝብ ነው ክርስቶስ የመጣው፤ ቀድሞ ዮርዳኖስን መሻገር አልችል ብሎ በባርነት ይኖር ወደ ነበረው ሕዝብ ሙሴ እንደተላከ ዛሬ ደግሞ ወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስ ወደዚህ ሕዝብ ተላከ፡፡ ከዚያ በፊት ኃጢአት፣ ሞት፣ ፍዳ ነግሠውበት የእነዚህ ሁሉ ምንጭ የሆነው ዲያብሎስ ሠልጥኖበት ክብረ ሥጋን፣ ክብረ ነፍስን፣ ነጻነትን፣ ሰማያዊት ርስትን ተነጥቆ ከሞት ጋር ተላምዶ መቃብር የመጨረሻ ዕጣ ፋንታው ሆኖ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል፡፡
ነገር ግን አሻጋሪያችን ክርስቶስ በእለተ ጽንስ ቁራኝነትን፣ በእለተ ልደት መርገምን፣ በእለተ ስቅለት ኃጢአትን ሞትን ፍዳን አጥፍቶ ወደ መቃብር ወርዶ በመቃብር ባደረባቸው ሌሊቶች ሙስና መቃብርን አጥፍቶ በሦስተኛው ቀን ተነሥቷል፡፡ የሰው ልጅ ከሀሳር ወደ ክብር፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ፣ ከሞት ወደ ሕይወት መሻገሩን ያረጋገጥነው በዚሁ እለት ነው፤
በመቃብር ፈርሶ በስብሶ ቀርቷል እንዳንል መቃብሩ ባዶ ሆኗል፤ ማቴ 28÷5፣ ሞት ሠልጥኖበታል እንዳንል መግነዙ ተፈቷል፤ የአይሁድን ቃል ሰምተን ደቀ መዛሙርቱ ሰርቀው ወስደውታል እንዳንል ‹‹ተነሥቷል በዚህ የለም›› ማር 16÷5 የሚለው የመላእክት ምስክርነት ተሰምቶለታል፡፡ ሁሉም ነገር በዚህ ቀን አዲስ ነው፤ እንደ አይሁድ ሥርዓት ሴቶቹ ይዘውት የመጡትን ሽቱ የሚቀቡት ሬሳ በመቃብር ውስጥ ማግኘት አይቻልም፤

Tuesday, 5 January 2016

ነገረ ቤተ ክርስቲያን-- ክፍል ሰባት



ያልጠበቅናቸው ሦስቱ ቦታዎች

ባለፈው ክፍለ ትምህርታችን ነገረ ማኅሌትን አንስተን ቤተ ክርስቲያናችን በቅኔ ማኅሌት ውስጥ የክርስቶስን የእለተ ዓርብ ስቃይ በአገልግሎቷ እንዴት እንደምትገልጥ አይተን ነበር በዚህም ቤተ ክርስቲያናችን ከመስቀሉ በቀር ሌላ አጀንዳ እንደሌላት ግንዛቤ ወስዳችኋል ብየ አስባለሁ፡፡ ለዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ነገር ግን ያልጠበቅናቸው ሦስት ቦታዎችን እናያለን ረድኤተ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ትሁን፡፡

ሦስቱ ቦታዎች ያልናቸው የዘወትር አገልግሎታችን የሚፈፀምባቸው ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ደጅ የምንጠናባቸው ቦታዎች ናቸው እነርሱም፡-
Ø  መካነ ጸሎት
Ø  መካነ ተግሣጽ
Ø  መካነ ምጽዋት ናቸው
፠ መካነ ጸሎት:-  የምንለው ከቤተ መቅደስ እስከ ቅኔ ማኅሌት ያለውን ነው፡፡ በፍት. መን. አን. 13 እንደ ተደነገገው በቤተ መቅደስ ውስጥ ከዲቁና እስከ ፕትርክና ድረስ መዓርገ ክህነት ያላቸው አበው ለጸሎት ይቆሙበታል፡፡ ነገሥታቱም መዓርገ ክህነት ያላቸው ከሆኑ በዚህ ሥፍራ እንዲጸልዩ ተፈቅዷል፡፡ ነገር ግን በዚህ ሥፍራ ለጸሎት ብቻ ካልሆነ ለሌላ ለምንም ነገር መግባት አልተፈቀደም ገብቶ መቀመጥ ዋዘዛ ፈዛዛ ማውራት እንዳይገባ ተጽፏል፡፡ ምክንያቱም ቦታው አትናቴዎስ በቅዳሴው እንደ ተናገረው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገባበት በበጎ አገልግሎት ያገለገሉትን ካህናቱን እና ዲያቆናቱን በቀኝ እና በግራ አድርጎ ምሥጢር የሚያሳይበት የደብተራ ብርሃን ምሳሌ ነውና፡፡ ያን ጊዜ ዋዛ ፈዛዛ መች አለና! ያንጊዜ መቀመጥ ማንቀላፋት መቸ አለና! ስለዚህ በዚህ ሥፍራ የምንቆም ሁላችን መጠንቀቅ እና የቆምንበትን ቦታ ማስተዋል ይገባል፡፡
ከቤተ መቅደስ ቀጥሎ ባለው ክፍል ለሥጋው ለደሙ የተዘጋጁ ምዕመናን የሚቆሙበት ሲሆን ወንዶችም ሴቶችም በየነገዳቸው ለጊዜው የሥጋው የደሙን መድረስ ፍጻሜው ግን የክርስቶስን መምጣት ተስፋ እያደረጉ ደጅ የሚጠኑበት ቦታ ነው፡፡ እስከ ቅዳሴው መጀመር ድረስ የግል ጸሎታቸውን የሚያደርሱትም በዚህ ሥፍራ ነው፡፡
ከዚህ ሥፍራ በኋላ የምናገኘው ቅኔ ማኅሌቱን ሲሆን የዚህ ሥፍራ ባለቤት የለውም ማለትም እስካሁን ያልናቸው ካህናትና ምእመናን ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚቆሙበት አንጅ ከነዚህ የተለየ ፆታ ምእመናን ስለሌለ ነው፡፡